Monday, November 4, 2013

ከዓይን ላይ የሚነሣ መንፈስ (ቡዳ)



ከዓይን ላይ የሚነሣ መንፈስ (ቡዳ) ሰዎችን የተለማመደ ለዘናት ከሰው ልጆች ጠባይ ጋር ተመሳስሎ የኖረና ዘሩ ያደረገ ዓይነቱ ይለያይ እንጂ ሰውን በከፍተኛ ደረጆ የማጥቃት ልምድ ያካባተ የቱጋ ይዞ መቼ እንደሚጥል መረጀ ያለው ከመተቶች ሁሉ በበለጠ ሁኔታ የከፋ ጉዳት የሚያደርስ ከአንድ ወደ ሌላው ረቀቅ ባለ ችሎታ የሚተላለፍ አደገኛ የሆነ መንፈስ ነው : : ከዓይን ላይ የሚነሣ መንፈስን በአጭሩ (ቡዳ) በማለት ይጠራል : :

( የመንፈሱ የመግቢያ አቅጣጫዎች )

- ከቤተሰብ የሚወረስ ዛር ብዙ ጊዜ የቡዳ መንፈስ መነሻው ከእናት : ከአባት : ከአያት :
ከቅድመ አያት : ከቅም አያት ወዘተ . . . ሲወርድ ሲዋረድ የመጣ ዛር ሲሆን በመዋለድ በአካል በደምና በነፍስ ውስጥ ተዋሕዶ እየተወራረሰ እንደ ልክፍት የሚይዝ ነው : :

- በሌሎች ላይ የሚያርፍ መንፈስ ይህ ከመነሻው ተሸጋጋሪ ሳይሆን ከውጪ ወደ ውስጥ በዓይን አማካኝነት ወደ ሌሎች የሚሄድና በሌሎች ላይ የሚያርፍ መንፈስ ሲሆን በሇላም ተመልሶ ከውሰጥ ወደ ውጭ ሌላውን ለመብላት የሚንቀሳቀስ ጠላት ነው : : ከሰባት ዓመት በሇላ ግን ራሱ ቡዳው ተሻጋሪ መንፈስ ይሆናል : : መንፈሱ በሰውነትችን ውስጥ ሥፍራ የሚዘው በሶስት ባታዎች ላይ ነው : :

1. በደም ውስጥ

2. ሥጋ ላይ

3. ነፍስ ጋር

* በደም ውስጥ የሚቀመጥ የቡዳ መንፈስ በደም ውስጥ የተዋሐደው ይህ መንፈስ አንዳንድ የደም ግብሮችን የለመደና የሚጠይቅ ዶሮ : በግ ወዘተ . . . እረዱልኝ
የሚል አልፎ ተርፎም አምባ ጐር አስነስቶ በዚሁ ጸብ ሣብይም ደም ማፍሳስ ደም ሲፈስ ማየት የሚፈልግ መንፈስ ነው : : በዝህም ምክንያት የቡዳውና መንፈስ ተለውጦ
የዛሩን ጠባይ ይወርሣል ማለት ነው : :

* ሥጋ ላይ ያለ የቡዳ መንፈስ ዓይን ላይ ተቀምጦና ከዐዓን ላይ እየተነሣ ሌሎችን
ለማጥቃት የሚሰማራ መንፈስ ነው : :

* ከነፍስ ጋር የተዋሃደ የቡዳ መንፈስ በዚሀ ሄደት ክፉው መንፈስ መቶ በማቶ ከነፍሳችን ጋር ተዋሕዷል ማለት ነው : :

ይህንን ከውሰጣችን ለመለየት ብዙ ጊዜ ያየሚፈጅ ሲሆን ተከታታይ " የቅድስ ቁርባንና" የጸሎት ሥርዐት ያስፈልጋል : : ምክንያቱም ነፍሳችንና መንፈሱ አንድ
በመሆናቸው ነው : : ይህ ከነፍስ ጋር የተዋሃደ መንፈስ ሥር የሰደደ መሰረት ስለያዘ ጥቃቱ ከበድ የለ ነው : :

በዚህ ዘመን ከነፍስ ጋር በፍጥነት ለሚዋሃዲ መንፈሶች ምሳሎ የሚሆኑን የመናፍቅና የዶ/ር ራምፓና የኦሾ የሣይኮሎጂ መንፈሶች
ናቸው : :

{ የመንፈሱ የጥቃት መንገዶች }

- የራሱን የሰውየውን ነሮ የሚበላ መንፈስ
ገንዘቡን ጊዜውን በአጠቃላይ በረከቱን ሁሉ እየበላ ዕድሜ ልኩን እንደባዘነ እንደደከመና እንደባከነ እንዲኖር ያደርገዋል : :

- ዕድልን የሚበላ መንፈስ ሁልጊዜ ከጠማማ ከክፉ ከሙዋርተኛና ጠባዩን ከሚያበለሽ ሰው
ጋር የሚያገናኝ መንፈስ ነው : :

በአጠቃላይ ዕድሉ ከመጥፎ ሰው ጋር ስለሚያውለው የራሱ ጠባይ ወደ ክፉት ያዘነበለ ይሆናል : :

- እየበላ የሌሎችን ሕይወት የሚያበላሽ የቡዳ መንፈስ ከላይ የተጠቀሱት ሁለቱ የቡዳ የጥቃት መንገዶች ከአካላዊ ጤና ጋር በቀጥታ የተገናኘ ጉዳት የማያደርሱ ሲሆኑ ይህ ሶስተኛው መንፈስ ግን አካልን የሚይዝ የሚበላ ጤናን የሚያውክና አዚም የሚሆን መንፈስ ነው : :


ማንኛውም ሰው በቡዳም ይበላ በመተትም ይታሰር በአጋንትም ይያዝ በአስማተኞችም ይጠለፍ በመስተ-ፈቅርም ይግባ ከሰባት አመት በዋላ ግን ያሰው ወደ ቡዳነት ይለወጣል እናት ልጇን ምን ብትወደው እርሷ ላይ ባለው መንፈስ አማካኝነት ልጇን ራስዋ ትበላለች በሌላ አነጋገር እርሷ ላይ ያለው መንፈስ ልጇን አጠቃው (በላው) ማለት ነው : :

በሌላ በኩል ደግሞ በሰው ሕወት ውስጥ የሚገባው ይህ መነፈስ የሌሎችሰዋችን ባሕርይ ይዞ ስለሚመጣ አንዳንድ ለየት ያሉ
ጉዳቶችን ሲያስከትሉ እናያለን

<ለምሳሎ > ለምጽ እና የቡዳ መንፈስ ያለባት ሴት መንፈሱ ያንን ለመጽ የፈጠረባትን ችሎታና ሀይል ያወቀና የተረዳ ስለሆነ ሌላ ሰው ላይ ሄዶ በሚያርፍበት ጊዜ ለምጹን እዚያ ሰው ላይ ያሳያል : :

በሌላ አገላለጽ በመንፈሱ የውጊያ ሥልትና ጥቃት መሰረት በበይው ላይ ያለው ለምጽ በተበይው ላይ ይታያል ይወጣል ማለት ነው : :

ሰውየውን የበላው መንፈስ እጅግ በጣም ጅል ከሆነ ደግሞ በብዳ የተበላው ሰው የቀድሞው የራሱ ባሕሪይ ይጠፋና ፍጽም ጅልና አዝም የተጫነው ይሆናል : : በዚህ ጊዜ ለተወሰነ ወቅት ግራ መጋባት : ተስፋ መቁረጥ : መናደድ : በሕይወትና በኑሮ ውስጥ አዚም እስኪ ጫነው ድረስ መቅበጥበጥ : አለመመቸት ወዘተ . , , የሚታይበት ሲሆን ሰባት አመት ከሞላው በዋላ ደግሞ ይህንኑ መንፈስ ለልጆች ሲያካፍልና ሲያስተላልፍ
ይታያል : :

መጽሐፍ ቅዱስ በትንቢት ዘካሪያስ

" የሰው ጠላቱ ቤተሰቡ ይሆናል "

በማለት የሚገልጸው አንድም ይህንን የውርስ ክፉ መንፈስ ጠባይን ለማመልከት ነው : : እንዲህ ዓይነቱን መከራ በክፉው መንፈስ አማካኝነት ይታይባቸዋል ለመንፈሳዊ ነገር የሚሰጡት ግምት በዜሮ የተዛባ ነው : :

ለሥራ የሚሰጡት ትኩረት ጸሎት ከማድረስ የላቀ ነው : : ስለቅድስናና ሰማያዊ ነገር ሲነገራቸው ወዲያውኑ የተቃውሞ ድምጽ ያሰማሉ ሌላው ደግሞ ቅዱስ ወንጌሊ በሚነገርበት ጊዜ ለራሳቸው የሚመቻቸው ብቻ መርጠው ይሰማሉ : :

ነቅሰው የሚያስቀሯቸው ቃላቶች ይበዛሉ : : "ቅዱስ ቁርባን" ትልቅ ሥርየት እንደሆነ
ዲያብሎስን እንደሚቃወም የዘር መንፈስን እንደሚያቆም ወደ በረከት እንደሚመራ የሰማያዊ መንግሰት ልብስ እንደሆነ
ሲነገራቸው ይቃወማሉ ገና ውሰጤ አልተቀበለውም ይላሉ : :

- የሌሎችን ምክር አይሰሙም በራሳቸው መንገድ ብቻ ይመራሉ : : እነኚህን በመሳሰሉ ሁኔታዎች ውስጥ ኖረው የልጆቻቸውን የጉዞ አቅጣጫ ዞር ብለው ሲመለከቱ ደግሞ
የአብራካቸው ክፉዮች ስፈራቸውን ለቀዋል : : ከትክክለኛው የሕይወት ጎዳናቸው ጠፍተው ይኖራሉ : : ከልቦናቸውና ከክርስትና ሕይወታቸው ርቀዋል : : የራሳቸው ጠባይ ከቤተሰብ ከተወረሱት የመናፍስቱ አደጋ ጋር ተያይዞ እንደገና በአሰልቺ በአደናጋሪና ግራ በሚያጋባ ሕይወት ውስጥ እንዲባዝኑ
ያደርጋቸዋል : :

እነዚህ ሰዎች ልጆቻቸውን መምከር አይችሉም : : ሌላው ቀርቶ አባት ለልጁ ይሄ ነገር ይጠቅምሃል ብሎ ቢነግረው እንኯን በልጅየው በኩል ተቀባይነት አያገኝም : :
በተያያዘ ሁኔታ ሌላ ላይ የማረፍና ሌላውን የመያዝ ችሎታው የተለያየ ነው : : አንዳንዱ ወድያውኑ ውስጥ ገብቶ ሕይወቱና ዕድል ላይ ጥናት ያደርጋል : : መናፍስቱ ውስጣችን ከገቡ በዋላ ዕድሉ እንዴት ነው ? ተስፉው እንዴት ነው ? እውቀቱ እንዴት ነው ? የቱን ልያዘው ? የት ሲደርስ በአጭር ልቅጨው ? የትኛው መሥሠር ላይ ሊበሳጭ ይችላል ወዘተ. . . በማለት የሚበላውን ሰው ሆኔታ ረዘም ላለ ጊዜ ሲያጠኑ ይቆያሉ : :

ከነዚህ ውስጥ በተሊይ ተበላጭተን እግዚአብሔርን የምናማርርበትን ወቅት ዳያብሎስ በክፍተኛ ደረጃ ይፈልገዋል
ይመዘግበዋል : : ምክንያቱም ይህ ወቅት ሰይጣን ወጥመዱን ለመዘርጋት አመቺ ሁኔታ ስለሚፈጥርለት ነው : :

በእነዚህ ጠባያት የተነሣ የክፋው መንፈስ የውጊያ ሥልትና ጥበብ ከዘመኑ ጋር እኩል እያደገና እየተለዋወጠ መጥቷል የመናፍስቱ
አደገኛና አስገራሚ ተፈጥሮ በዋናነት ከዚህ ይመነጫል : :

መጽሐፍ ቅዱስ ክብደት ባለው ሁኔታ

" ከእግዚአብሔር እንደሆንን ዓለም በመላው በክፉ እንደተያዘ እናውቃለን " በማለት 1 ዮሐ 5:19 ላይ

የገለጸው የዚህን ነጥብ እውነታ ለማረጋገጥ ነው : : ከዝህ በተጨማሪ ይህ ቃል የሚያመለክተን አብዛኛው መናፍስቱ
በዓለም ላይ ለማሸነፍ ያላቸው ዕድል በጣም ሰፊ መሃኑን ነው : :

" በዚህ ዓለም እንዳለው ኑሮ በማይታዘዙትም ልጆች ላይ አሁን ለሚሰራው መንፈስ አለቃ እንደሆነው በአየር ላይ ሥልጣን እንዳለው አለቃ ፈቃድ በፈት ተመላለሳችሁባቺው " ኤፌ 2 : 2

ቡዳው ሌላውን በልቶ ቡዳ ካደረገው ዛሩ ለብቻው ራሱን የቻለ ቡዳ ከሆነና የተፈጥሮው ቡዳ በክፍተኛና በሙሉ ሀይሉ ከተነቃነቀ ዓለም በመላው በክፉ እንደቲያዘ እናውቃለን ማለት ነው : :

{ የተፊጥሮ ቡዳ }

የተፈጥረሮ ቡዳ ማለት መቶ በመቶ ከአጋንንቱ ጋር የተወራረሰ ማለት ነው : : እነዚህም ከመናፍሰቱ ጋር ለረዥም ዘመናት
ቤተሰብ ሆነው የኖሩና የተጋቡ ጸሎትና ቡተክርስቲያን የማይስማማቸው በአንጻሩ ደግሞ የሚናፍስቱ ኑሮ ብቻ የሚመቻቸው ከዲያብሎስ ጋር የተቆራኙት : ሟርተኞች :
ጠንቇዮች : አስማተኞች :ጥላወጊ : አንደ ርቢ ለመሳሰሉት የክፉ መናፍስ አገልጋዮች ናቸው : :

{ የሳጥናኤል ሠራዊት }

* ባጀት አይፈልጉም የሚንቀሳቀሱት በአንተ በጀት ነው : :

* ቢሯቸው አይዘጋም ምን ጊዜ ምክፍት ነው : :

* አያንቀላፉም መዘናጋት በእነርሱ ዘንድ የለም : :

* አያረጁም ጡረታ አይወጡም

* በፓሊስ አይያዙም በፍርድቤት አይዳኙም

* አይቀበሩም ወደ ሲኦል ተሸኝተው ካልታሰሩ በስተቀር አይሞቱም : :